“በበረሃ አሸዋ ውስጥ የወርቅ ሐይቅ ከቀዝቃዛ ትኩስ ምንጭ ያነሰ ነው፤ ለጠፋ በግ ደግሞ እረኛ ልጅ ከባለጸጋው ንጉሥ ይበልጣል” እንደሚባለው፣ በዚህች ምድር ላይ ዋጋ ያለውና በመንግሥተ ሰማያት ዋጋ ያለው ነገር በእጅጉ ይለያያል። በዓለም ላይ ያሉ ብዙ ሰዎች የሚያከብሩት ሀብት፣ ክብርና ኃይል በመንግሥተ ሰማያት ዋጋ የላቸውም። ለዚህም ነው የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን በስደት ውስጥ እንኳን ለመንግሥተ ሰማያት የኖሩት።
በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ፣ እጅግ ዋጋ ያለው ሥራ የእግዚአብሔርን ቃል በተግባር ላይ ማዋል ነው። የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አባላት በአዲሱ ኪዳን እውነት አንድ የጠፋ ነፍስ እንኳን ይፈልጋሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል በመንግሥተ ሰማያት እንደ ነገሥታት እንደሚገዙና እንደ ከዋክብት ለዘላለም እንደሚያበሩ ያምናሉ።
እነዚህ ሁሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ሳያገኙ እምነታቸውን እንደ ጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከሩቅ አይተው ሰላም አሉት፤ በዚህ ምድር ሲኖሩ መጻተኞችና እንግዶች መሆናቸውን ተገንዝበው ነበርና። ዕብራውያን 11:13
ጥበበኞች እንደ ሰማይ ጸዳል፣ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ። ዳንኤል 12:3
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት